ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከ300 ሺህ በላይ በግጭት በአየር ንብረት ለውጥ እና በኑሮ ውድነት ሳቢያ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ህጻናት በተፋጠነ የትምህርት መርሃግብር አማካኝነት፤ለአንድ ዓመት ያህል አስተምሮ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በመፈተን ከእድሜ እኩዮቻቸው እኩል ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪም በግጭት እና በሀገር ውስጥ መፈናቀሎች ምክንያት ለአዕምሮ ጠባሳ እና እንዲሁም ለድህረ አደጋ ሰቀቀን የተጋለጡ መምህራንን እና ተማሪዎችንም ያግዛል። ኤደን ገረመው የተቋሙን የምሥራቅ አፍሪካ ዲሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ኃይሉን እንዲሁም በትግራይ ክልል እና ድሬዳዋ ከተማ ያሉ እናቶችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።
በግጭት ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ህጻናትን ከእኩዮቻቸው እኩል የሚያደርገው ተቋም
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሜይ 15, 2024
የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን ዐዋጅን ያሻሽላል የተባለ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ
-
ሜይ 15, 2024
የ16 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የፒኤችዲ ተማሪ ፀረ ቲቢ እንቅስቃሴ
-
ሜይ 15, 2024
በኢታንግ ልዩ ወረዳ ግጭት 11 ሰዎች ሲገደሉ በሺሕዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ