በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል


በጋዛ ሰርጥ እ.አ.አ ሚያዚያ 27፣ 2024 በእስራኤል የተፈጸመ ድብደባን ያሳያል (ፎቶ ኤኤፍፒ)
በጋዛ ሰርጥ እ.አ.አ ሚያዚያ 27፣ 2024 በእስራኤል የተፈጸመ ድብደባን ያሳያል (ፎቶ ኤኤፍፒ)

በጋዛ ተኩስ ማቆም ላይ እንዲደረስና በሐማስ የተያዙ ታጋቾች እንዲለቀቁ ለማስቻል ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ዛሬ እሁድ እየቀጠለ ባለበትም ወቅት፣ እስራኤል በግዛቲቱ ላይ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት ቀጥላለች፡፡

በሐማስ የተያዙ ሁለት ታጋቾችን ያሳያል የተባለ ቪዲዮ መለቀቁን ተከትሎ፣ በእስራኤል ቁጣው አይሏል። ተቃዋሚ ሰልፈኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ግፊት በማደረግ ላይ ናቸው።

በጋዛ የሚታየውን ሰብ ዓዊ ሁኔታ በተመለከተ ዓለም አቀፍ ተቃውሞውም እንደቀጠለ ነው። እስራኤል በምድር ራፋን የምትወር ከሆነ ሰብዓዊ ቀውሱ እንደሚከፋ እና ብዛት ያላቸው ሲቪሎች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የዓለም መሪዎች እና የዕርዳታ ድርጅቶች በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፈረንሣዩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስቴፋን ሴዡኔ ዛሬ ሌባኖስ ገብተዋል። በእስራኤል እና በሌባኖስ ድንበር መካከል ያለው ግጭት እንዲረግብ ጥረት ለማድረግ ነው ተብሏል። የሌባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ፣ በየቀኑ በሚባል ደረጃ ከእስራኤል ኃይሎች ጋራ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ በማድረግ ላይ ነው።

የፍልስጤማውያኑ ፕሬዝደንት ሞሃሙድ ሐባስ፣ እስራኤል ራፋን ከመውረር እንድታስቆም ዛሬ እሁድ አሜሪካንን ተማጽነዋል። እስራኤል በራፋ ወረራውን የምትፈጽም ከሆነ፣ “በፍልስጤማውያኑ ታሪክ ከባድ ዕልቂት” ይሆናል ብለዋል ሃባስ።

ሐማስ ከዚህ በፊት ቋሚ የተኩስ ማቆም እንዲደረግ ቢጠይቅም፣ እስራኤል ሳትቀበለው ቀርታለች፡፡

‘አክሲዮስ’ የተሰኘው የዜና አውታር ሁለት የእስራኤል ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዛሬ እንደዘገበው፣ ታጋቾቾ ከተለቀቁ በኋላ በጋዛ “ዘላቂ ፀጥታ” እንዲኖር እስራኤል ሃሳብ አቅርባለች፡፡

ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ እስራኤል ተኩስ ለማቆም ፍንጭ ስትሰጥ የመጀመሪያው ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG